ሰላምን የመረጡ የታጣቂ መሪዎች እና አባላቱ ወደ አካባቢያቸው ተመለሱ።

46

ደብረ ብርሃን: ሐምሌ 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ሸዋ ዞን በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ሰላምን መርጠው ወደ አካባቢያቸው ተመልሰዋል።

ታጣቂዎቹ ለማኅበረሰባቸውም ይሁን ለራሳቸው ከችግር ውጭ ያተረፉት ነገር ባለመኖሩ ሰላማዊ መንገድን መምረጣቸውን ነው የተናገሩት።

ታጣቂዎችን ይመራ የነበረው አለሙ ሃብቱ የወጡበት ትግል ዓላማ የሌለው እና የግል ጥቅም ማሳደድ ላይ በመጠመዱ ስህተት መኾኑን አምኖ ሰላምን በመምረጥ ከሚመራቸው ጓደኞቹ ጋር ወደ ቀየው መመለሱን ነው ያብራራው።

የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር ንጉሴ ሞገስ በዞኑ በርካታ ታጣቂዎች ወደ ማኅበረሰባቸው እየተመለሱ ነው ብለዋል።

ዛሬ ላይ ሰላም መርጠው ወደ ሕዝብ እና መንግሥት የተመለሱ 13 የታጣቂ ቡድኑ መሪ እና አባላት መኾናቸውን ተናግረዋል።

ታጣቂዎቹ አንድ ዲሽቃ፣ አራት ብሬን፣ አንድ ስናይፕር፣ አምስት ክላሽ፣ አምስት የቃታ መሳሪያ ከበርካታ ተተኳሾቻቸው ጋር ይዘው ነው ወደ ሰላም የተመለሱት።

በሰላም ሕዝባቸውን ለመካስ ለሚመለሱ አስፈላጊው እንክብካቤ ተደርጎ ሰላማዊ ሕይወት እንዲቀጥሉ ይደረጋልም ብለዋል ኮማንደር ንጉሴ።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየተዳፈነው እሳት
Next articleትብብር እና ቅንጅት የማኅበረሰብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው።