
ባሕር ዳር: ሐምሌ 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የጭስ አልባው ኢንዱስትሪ ተጨማሪ ከፍታ የኾነችው ጣናነሽ ቁጥር ፪ ውጣ ውረድ የበዛበትን እጅግ አስቸጋሪ የዓባይ በርሃ ጉዞዋን ጨርሳ ደጀን ከተማ ደርሳለች።

ጀልባዋ ደጀን ከተማ ስትደርስ በደጀን ወረዳ፣ በደጀን ከተማ አስተዳደር፣ በአዋበል ወረዳ፣ በሉማሜ ከተማ አስተዳደር እና በዞኑ የመንግሥት ከፍተኛ ሥራ ኀላፊዎች እና በአካባቢው ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላታል።

ለቱሪዝም ሃብት ተጨማሪ ገጸ በረከት ኾና የመጣችው ጣናነሽ ቁጥር ፪ ጀልባ ጣና ሐይቅ ለመድረስ 335 ኪሎ ሜትር ብቻ ቀርቷታል።
በአንድ ጊዜ 188 ሰዎችን የማጫን አቅም ያላት ጣናነሽ ቁጥር ፪ መዳረሻዋ በኾነው ጣና ሐይቅ እስከምትደርስ ድረስ በደረሰችባቸው አካባቢዎች ሁሉ ደማቅ አቀባበል እንደሚደረግላት ይጠበቃል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

