ዩኒቨርሲቲዎች የፋሲለደስ ስምምነትን ተፈራረሙ።

104

ጎንደር: ሐምሌ 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቃል ኪዳን ቤተሰብን ተሞክሮ በመውሰድ በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ለማስፋፋት ዩኒቨርሲቲዎች የፋሲለደስ የቃል ኪዳን ስምምነትን ተፈራርመዋል።

የፋሲለደስ የቃል ኪዳን ስምምነት የኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስትር ሙሐመድ እድሪስ በተገኙበት ነው የተፈረመው።

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቃል ኪዳን ቤተሰብ ከተመሠረተ ከስድስት ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ሲኾን ከሀገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች የሚመጡ ተማሪዎችን በመቀበል በጎንደር ከተማ ቤተሰብ እንዲኖራቸው በማድረግ ሲሠራ ቆይቷል።

ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ 26 የአዋጅ ድንጋጌዎች ላይ ማሻሻያ አድርጓል።
Next articleከ1ሚሊዮን በላይ ለሚኾኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል።