“የአንድነታችን አርማ የኅብረታችን ካስማ በኾነው ባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም አረንጓዴ አሻራችንን አስቀምጠናል” ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)

5

ባሕር ዳር: ሐምሌ 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና ሌሎች የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ መሪዎች በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡

በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ከባሕር ዳር ከተማ ሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ወጣት ስፖርተኞች እና የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሠራተኞች ተሳትፈዋል፡፡

“በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሃሳብ በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ላይ የተገኙት የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ መሪዎች ከታዳጊ ስፖርተኞች ጋር በጋራ ችግኝ ተክለዋል ያሉት የክልሉ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኀላፊ እርዚቅ ኢሳ መርሐ ግብሩ ለተተኪ ወጣቶቹ ልዩ ትርጉም አለው ብለዋል፡፡ ከባሕር ዳር ከተማ ሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ታዳጊ ስፖርተኞች የስታዲየሙን የግንባታ ሂደት ተዘዋውረው መጎብኘታቸውንም ቢሮ ኀላፊው ጠቁመዋል፡፡

“የአንድነታችን አርማ የኅብረታችን ካስማ በኾነው ብሔራዊ ስታዲዮም አረንጓዴ አሻራችንን አስቀምጠናል” ያሉት በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) መርሐ ግብሩ አሻራን ለትውልድ የማስተላለፍ ሂደት ነው ብለዋል፡፡

የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዬም ግንባታ ሲጠናቀቅ በየጊዜው ዓለምን ተቀብለን የምናስተናግድበት መድረክ ነው ሲሉም ተናግረዋል። የግንባታ ሂደቱ በተቀመጠለት መርሐ ግብር እንዲጠናቀቅ የክልሉ መንግሥት ድጋፍ እና ክትትል አልተለየውም ነው ያሉት፡፡ ጎን ለጎን ደግሞ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር መካሄዱ ለአስፈጻሚው አካል ክትትል፤ ለወጣቶቹ ደግሞ ተስፋ የሚኾን ነው ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየባሕላዊ ሕክምና መድኃኒቶች ላይ በትኩረት መሥራት ይገባል።
Next articleየመስኖ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜ ማጠናቀቅ መቻሉን የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር አስታወቀ።