በደብረ ብርሃን ከተማ 25 ኢንዱስትሪዎች ወደ ማምረት ተሸጋግረዋል።

16

ደብረ ብርሃን: ሐምሌ 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ግዙፍ ፋይዳ ያላቸው 25 ኢንዱስትሪዎች ወደ ምርት መግባታቸውን የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ገልጿል።

መምሪያው የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅ መድረክ እያካሄደ ነው።

የመምሪያው ኀላፊ ብርሃን ገብረ ሕይወት በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት 200 ያህል ባለሃብቶች በከተማዋ ያሉ አማራጮችን ተጠቅመው መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ የሚያስችል ሥራ መከናወኑን ተናግረዋል።

በ2017 የበጀት ዓመቱ መጨረሻ ድረስ 36 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 252 ባለሃብቶች ፈቃድ መውሰዳቸውን አንስተዋል።

እነዚህ ባለሃብቶች ሙሉ በሙሉ የማምረት ሥራ ሲጀምሩ ለ 21 ሺህ ሰዎች የሥራ እድል መፍጠር የሚችሉ መኾናቸውን ጠቁመዋል።

አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ከመስጠት ባሻገር 25 ኢንዱስትሪዎችን ወደ ምርት ሥራ ማስገባት ተችሏል ነው ያሉት ኀላፊው።

ወደ ምርት የገቡት ፋብሪካዎችም ለ5 ሺህ 200 የአካባቢው ነዋሪዎች የሥራ እድል ፈጥረዋል ነው ያሉት።

የሰላም እጦቱ ፈታኝ ቢኾንም ችግሩን ተቋቁሞ ተኪ ምርት በማምረት፣ የኢንዱስትሪ ምርቶችን ለውጪ ገበያ በማቅረብ የውጪ ምንዛሬ በማስገኘት እና በሥራ እድል ፈጠራ አመርቂ ውጤት የተመዘገበበት እንደኾነም አቶ ብርሃን ገልጸዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleእርስዎ በዓመት ስንት ጊዜ ቅድመ ምርመራ ያደርጋሉ?
Next articleየአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች በወቅታዊ እና የክረምት ሥራዎች ዙሪያ እየተወያዩ ነው።