የወይዘሮ ስኂን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።

22

ደሴ: ሐምሌ 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የወይዘሮ ስኂን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።

የወይዘሮ ስኂን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን ሰለሞን ይመር በ2017 ዓ.ም ከደረጃ 2 እስከ ደረጃ 5፣ በረጅም እና አጭር ጊዜ ሥልጠና በ7 የሙያ እና የትምህርት ዘርፍ ያስተማራቸውን 734 ተማሪዎችን ማስመረቃቸውን ተናግረዋል። ከተመራቂዎቹ መካከል 203 የሚኾኑት ሴቶች መኾናቸውንም ገልጸዋል።

ተመራቂ ተማሪዎች ያገኙትን የንድፈ ሀሳብ እና የተግባር ዕውቀት ወደ ውጤት በመቀየር ተመራጭ እና ተፈላጊ መኾን እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በምረቃ ስነ ሥርዓቱ የደሴ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ እና የወይዘሮ ስኂን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የቦርድ ሰብሳቢ ሳሙኤል ሞላልኝ ባስተላለፉት መልዕክት ተመራቂዎቹ ለተመረቃችሁበት የሙያ መስክ ክብር በመስጠት ማኅበረሰቡን ልታገለግሉ ይገባል ብለዋል።

ሥራ ፈጣሪ እንጂ ሥራ ጠባቂ ባለመኾን ለለውጥ ተግቶ መሥራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

ዘጋቢ:- ተመስገን አሰፋ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“ሁሉን ተመራመሩ፤ የሚጠቅመውን ያዙ” ዶክተር አብርሃም አስናቀ
Next articleየአማራ ክልል መሬት ቢሮ የመሬት መረጃ አያያዝ ሥርዓትን ለማዘመን እየሠራ ነው።