
ባሕር ዳር: ሐምሌ 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ70 ዓመታት የዩኒቨርሲቲ እና በ100 ዓመታት የዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ዘመናቱ ለሀገር እና ለሕዝብ አበርክቶው ከፍተኛ ነው።
በዘመኑ ከ107 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ያስመረቀው የሰላሙ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ እያካሄደ ባለው የተማሪዎች ምረቃ ሥነ ሥርዓት የቀድሞ ተማሪዎችንም በድጋሜ አስመርቋል።
የቀድሞ ምሩቃኑ በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ እና በመላው ዓለም ታላላቅ አበርክቶዎችን ያደረጉ ናቸው። አሁንም አስተዋጽኦ እያደረጉ ነው።
በዛሬው የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተከፈተው ኦኮፔሽናል ቴራፒ የሠለጠኑ ተማሪዎች ተመርቀዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን