
ባሕር ዳር: ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ትምህርት መምሪያ የ2018 ዓ.ም የመማር ማስተማር ሥራ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በተመለከተ ከመንግሥት እና ከግል ትምህርት ቤት ከተውጣጡ መሪዎች ጋር በባሕር ዳር ከተማ ውይይት አካሂዷል፡፡
በውይይቱ የ2017 ዓ.ም ክፍተቶችን በማረም የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሥራን መሰረት የምንጥልበት ነው ያሉት የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ትምህርት መምሪያ ኀላፊ ሙሉዓለም አቤ (ዶ.ር) ናቸው፡፡
በዚህም በክረምት የበጎ ፈቃድ የቅድመ ዝግጅት ሥራ በመሥራት ለቀጣይ መማር ማስተማር ሂደት ምቹ ኹኔታዎችን መፍጠር ነው ብለዋል፡፡
2017/ለ2018 የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በተመለከተ ቀደም ተብሎ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ችግኞችን በመትከል እና የተለያዩ መረጃዎችን በመሰብሰብ ሥራ ተጀምሯል፡፡
የትምህርት ቤት መሻሻል መርሐ ግብር ተጠሪ ማሩ ቸኮል የ2017 ዓ.ም የክረምት ወራት የዜጎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስፈጸሚያ ዕቅድ በሚል የተጋጀ ሰነድ አቅርበዋል፡፡
ሰነዱ የትምህርት ሥርዓቱ ውጤት እንዲያመጣ ከቅድመ አንደኛ ክፍል በመነሳት ሕጻናት የሚውሉባቸው ተቋማትን ምቹ እንዲኾኑ ማድረግ ነው።
ትምህርት ቤቶችን ምቹ ለማድረግ በቀጣይ በእቅድ ሊሠሩ የታሰቡ ሥራዎች በአቶ ማሩ በዝርዝር ቀርበዋል፡፡ ከነዚህም መካከል የተሰበሩ ወንበሮች እና መማሪያ ክፍሎችን መጠገን፣ የተለያዩ ግብዓቶችን ማሟላት፣ በየተቋማቱ ችግኞችን መትከል፣ የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት እና መሰል ተግባራት እንደሚሠሩ አሥገንዝበዋል።
በባሕር ዳር ከተማ የቁልቋል ሜዳ አንደኛ ደረጃ ትህርት ቤት ርእሰ መምህርት ሀገር ነቅዐጥበብ
ከሐምሌ 10 ጀም የመማሪያ ክፍሎች፣ የጥቁር ሰሌዳዎች፣ የወንበር እና የአጥር ጥገናዎችን እንሠራለን ብለዋል፡፡
ትምህርት ሲጀመር ደግሞ የተማሪዎች ንጹህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት እንዲኖር የተበላሹ ታንከሮችን የመጠገን እና የማጽዳት ሥራ ይሠራል ነው ያሉት፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!