” ዓመቱ እውነትም የኢትዮጵያ የማንሠራራት ዘመን መነሻ የሆነ ዓመት ነበር” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

26

ባሕር ዳር: ሐምሌ 11/2017 (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የ2018 በጀት ዓመት የማንሠራራት ጉዟችንን የሚያጸኑ አዳዲስ እመርታዎችን ለማስመዝገብ በጋራ የምንተጋበት ዓመት ነው ብለዋል።

የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸምን እንደመነሻ በመውሰድ በተዘጋጀው የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ከፌደራል ተቋማት መሪዎች ጋር ዛሬ ውይይት እየተካሄደበት መኾኑን ገልጸዋል።

የ2017 በጀት ዓመት በብዙ መልኩ የኢትዮጵያ የብልጽግና ታሪክ እጥፋት ነው፡፡ ዓመቱ እውነትም የኢትዮጵያ የማንሠራራት ዘመን መነሻ የሆነ ዓመት ነበር ነው ያሉት። የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድም እነዚህን መልካም አፈጻጸሞች መነሻ የሚያደርግ መኾኑን ገልጸዋል።

በበጀት ዓመቱ በኢኮኖሚው ዘርፍ የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም በማድረግ የከረሙ ስብራቶቻችን ጠግነናል፡፡ የሕዳሴ ግድብን አጠናቅቀናል፡፡ የጋዝ ፕሮጀክታችንንም እያጠናቀቅን እንገኛለን፡፡ በከተሞቻችን የጀመርናቸው የኮሪደር ልማቶች ውጤት ማምጣት ጀምረዋል፡፡ የገጠር ኮሪደርም ጀምረናል ብለዋል።

የ2018 በጀት ዓመት ግቦቻችንም እነዚህን መልካም አፈጻጸሞች መነሻ የሚያደርጉ፣ ካለፈው በላይ ትጋት እና ጥረት የሚጠይቁ ናቸው። ለብቻ መሮጥን ብቻ ሳይሆን ጠንካራ ቅንጅትንም ይፈልጋሉ ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ ዛሬ በእኛ እጅ ናት፡፡ በአዲሱ በጀት ዓመት የላቁ ድሎችን በማስመዝገብ የኢትዮጵያን ማንሠራራት የሚያውጀው ትውልድ አካል እንደሆንን በማመን ለበለጠ ስኬት በትጋት መሥራት ይኖርብናል ብለዋል በመልዕክታቸው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየደብረ ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት በሁሉም የጥገና ዓይነቶች ሥራዎችን እያከናወነ.መኾኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር አስታወቀ።
Next articleየጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ምሩቃን ቀንን እያከበረ ነው።