የደብረ ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት በሁሉም የጥገና ዓይነቶች ሥራዎችን እያከናወነ.መኾኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር አስታወቀ።

13

ባሕር ዳር: ሐምሌ 11/2017 (አሚኮ) የደብረ ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት በስሩ በሚገኙ አራት የጥገና ክፍሎች አማካኝነት በሁሉም የጥገና ዓይነቶች ሥራዎችን እያከናወነ መኾኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር አስታውቋል፡፡

በበጀት ዓመቱ 389 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የመንገድ ሽፋን ተጠግኗል። የአዲስ አበባ-ጎንደር ዋና መንገድ አካል በኾነው በደጀን – ባሕር ዳር የመንገድ ክፍል ውስጥ መጠነ ሰፊ የአስፋልት ጥገና ሥራዎችን መሥራት ተችሏል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የድንገተኛ ጥገና ሥራዎች በዋናነት በዓባይ ግድብ መዳረሻ እና በጢቅ ፈለገ ብርሃን የመንገድ ክፍሎች ተከናውነዋል። የድልድይ እና ከልቨርት ጥገና እና ማሻሻል ሥራዎች በተለይ በሦስቱ ክፍሎች (በደጀን፣ በቡሬ፣ እና በባሕር ዳር) በማከናወን የትራፊክ እንቅስቃሴውን ያለምንም ችግር ማሳለጥ ተችሏል ተብሏል።

ከዚህም ባሻገር ለረዥም ጊዜ ተበላሽቶ የቆየውን በማንኩሳ- ብርሸለቆ የመንገድ ክፍል የሚገኘውን የብርሸለቆ ማሠልጠኛ መዳረሻ ድልድይ እና የዘማ ወንዝ ድልድይን ከድልድይ እና ስትራክቸር ቡድን ጋር በጋራ በመኾን በአጭር ጊዜ ወደ ብረት ድልድይ (Bailey Bridge) የመቀየር ሥራ ተሠርቷል፡፡

ከኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ከትራፊክ ደኅንነት ጋር በተያያዘም በሁሉም ክፍሎች ሥራዎች የተሠሩ ተሠርተዋል። በተለይም በደጀን ሴክሽን ከዚህ በፊት ከነበረው በበለጠ መልኩ ሰፊ ሥራዎችን ማከናወን ተችሏል ነው የተባለው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleእርስዎ በዓመት ስንት ጊዜ ቅድመ ምርመራ ያደርጋሉ?
Next article” ዓመቱ እውነትም የኢትዮጵያ የማንሠራራት ዘመን መነሻ የሆነ ዓመት ነበር” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ