ሀገራዊውን የምክክር ጉባኤ ለማካሄድ አስቻይ ኹኔታዎች እንዲፈጠሩ እየተሠራ ነው።

13

አዲስ አበባ፡ ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተሠሩ ወቅታዊ ሥራዎችን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ቃል አቀባይ ጥበቡ ታደሰ ኮሚሽኑ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ተሳትፎ ለማጠናከር ከምክክሩ አቋርጠው ከወጡ ሦሥት ፓርቲዎች ጋር ውይይት ማድረጉን ገልጸዋል።

በዚህም ፓርቲዎቹ ቅድመ ኹኔታዎችን ማስቀመጣቸውን እና በጋራ ለመሥራት ፍቃደኛ መኾናቸውን መግለጻቸውን ተናግረዋል።

ቃል አቀባዩ የሴቶችን ተሳትፎ ትርጉም ያለው ከማድረግ አኳያ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሴት የኮከስ አባላት ጋር ተመሳሳይ ውይይቶች መደረጉንም ጠቅሰዋል።

በሕግ ጥላ ስር ያሉ ዜጎች ሀሳባቸውን እንዲያቀርቡ ከማድረግ አኳያም ከፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ከፍተኛ ኀላፊዎች ጋር ውይይት መደረጉንም አንስተዋል።

ዓለም አቀፍ አጋርነትን በማጠናከር ረገድም ከኖርዌይ አምባሳደር እና ከዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ የኢትዮጵያ ልዑክ ጋር ውይይት መደረጉን ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ላይ ጠቅሰዋል።

ኮሚሽኑ ለሚያካሂደው ውጤታማ ምክክርም የኖርዌይ መንግሥት እና ሕዝብ እንዲኹም ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ስትራቴጂካዊ ድጋፎችን ለማድረግ መግባባት ላይ ተደርሷልም ነው ያሉት።

ሀገራዊውን የምክክር ጉባኤ ለማካሄድ አስቻይ ኹኔታዎች እንዲፈጠሩም እየሠራ መኾኑንም ኮሚሽኑ ገልጿል።

ዘጋቢ፦ ቤተልሄም ሰለሞን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleከ5ቢሊዮን ብር በላይ በኾነ ወጭ የተገነቡ የትምህርት ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት ዝግጁ ኾኑ።
Next articleእርስዎ በዓመት ስንት ጊዜ ቅድመ ምርመራ ያደርጋሉ?