ከ5ቢሊዮን ብር በላይ በኾነ ወጭ የተገነቡ የትምህርት ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት ዝግጁ ኾኑ።

10

አዲስ አበባ፡ ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ ተገንብተው የተጠናቀቁ 150 የትምህርት ፕሮጀክቶችን ዛሬ መርቀዋል።

በከተማ አሥተዳደሩ የመማሪያ ክፍል ጥበት እና የግንባታ ጥራት ችግር መኖር በመማር ማስተማር ተግባሩ ላይ አሉታዊ ጫና ሲያሳድር መቆየቱን ከንቲባዋ አንስተዋል።

ይኹን እንጅ የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት አኹን ላይ ደረጃቸውን የጠበቁ መማሪያ ክፍሎችን በመገንባት አገልግሎት እንዲሠጡ እየተደረገ ስለመኾኑም ነው ያስገነዘቡት።

ከንቲባዋ እንዳሉት በ2017 በጀት ዓመትም ከ5 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጭ የተገነቡ 150 የትምህርት ፕሮጀክቶች ናቸው ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት የተደረጉት።

ከተመረቁት ፕሮጀክቶች
መካከል ደረጃቸውን የጠበቁ 14 አዳዲስ ትምህርት ቤቶች። በ64 ነባር ትምህርት ቤቶች ላይ የማስፋፋያ ሥራ መከናወኑንም ከንቲባዋ አንስተዋል።

ትምህርት ቤቶቹ የአይሲቲ ክፍሎች፣ ቤተ ሙከራዎች፣ የመመገቢያ አዳራሾች፣ ቤተ መጽሐፍቶች፣ የስፖርት ሜዳዎች፣ የመጸዳጃ ቤቶች እና የውኃ አገልግሎቶችን ያካተቱ ናቸው ብለዋል ከንቲባዋ።

ዘጋቢ፦ ቴዎድሮስ ደሴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleበላይ ጋይንት ወረዳ ሲናቆ ወንዝ የተገነባው 40 ሜትር ቦክስ ገርደር ኮንክሪት ድልድይ ተጠናቆ ለአገልግሎት ኾነ።
Next articleሀገራዊውን የምክክር ጉባኤ ለማካሄድ አስቻይ ኹኔታዎች እንዲፈጠሩ እየተሠራ ነው።