
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በክልሉ መንግሥት በጀት በደቡብ ጎንደር ዞን ላይ ጋይንት ወረዳ በተንጣለለው ሲናቆ ወንዝ ላይ የተገነባው 40 ሜትር ቦክስ ገርደር ኮንክሪት ድልድይ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ኾኗል።
በክልሉ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ አማካኝነት በጥጥራ-ዛጎች ፕሮጀክት በጥራትና በጊዜ የተገነባው ድልድይ ብዙ ፈታኝ ኹኔታን ተቋቁመው መሥራት በመቻሉ ለአገልግሎት ክፍት ኾኗል።
የድልድዩ መሠራት ማኅበራዊ መስተጋብርን ከማጠናከር በላይ የግብርና ሰብል ምርት፣ የእንስሳት ሃብት፣ የደን ልማት ሃብት እና የማዕድን ሃብት ፀጋዎችን በስፍት አውጥቶ ለመጠቀምና የገበያ ትስስርን የመፍጠር ፋይዳ አለው ተብሏል።
ለፕሮጀክቱ ሥራ መሳካት የዞንና ወረዳ አሥተዳደር አካላት፣ መንገድ መምሪያና መንገድ ጽሕፈት ቤት፣ የአካባቢው ማኅበረሰብ ትብብርና ድጋፍ የሚመሰገን መኾኑን ከመንገድ ቢሮ የተገኘ መረጃ ያሳያል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን