118 ፕሮጀክቶችን እየገነባ መኾኑን የምዕራብ ጎጃም ዞን እና አካበቢው አልማ ጽሕፈት አስታወቀ።

12

ፍኖተ ሰላም: ሐምሌ 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ከ232 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ 118 ፕሮጀክቶችን እየገነባ መኾኑን የምዕራብ ጎጃም ዞን እና አካበቢው አልማ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

ጽሕፈት ቤቱ 587 ሺህ 923 ነባር አባላትን በማፍራት በምዕራብ እና ሰሜን ጎጃም ዞኖች በራስ አቅም የመልማት ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።

ከ2015 በጀት ዓመት ጀምሮ የልማት ሥራውን በሚያከናውንባቸው አካባቢዎች 232 ሚሊዮን 807 ሺህ ብር ወጪ 113 ሕንፃ ትምህርት ቤቶችን እና አምስት ደግሞ የጤና ተቋማትን እየገነባ ነው ተብሏል።

ከነዚህም ውስጥ 16 ፕሮጀክቶች መጠናቀቃቸውን የዞን ልማት ጽሕፈት ቤት ዳይሬክተር ባንቴ ታደሰ ለአሚኮ ገልጸዋል።

በ2018 በጀት ዓመት በአይነት፣ በገንዘብ እና በሙያ ድጋፍ 348 ሚሊዮን ብር ሀብት በማሰባሰብ የተለያዩ የልማት ተግባራትን ለማከናወን አቅዶ ሥራ መጀመሩን ተናግረዋል።

በቀጣይ በጀት ዓመት ከሚሰበሰበው ሀብት 111 የቅድመ መደበኛ፣ የመጀመሪያ፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ዘጠኝ ደግሞ የሳይንስ፣ ኢንጅነሪንግ፣ የቴክኖሎጂ እና ሒሳብ/STEM ማዕከላትን ለመገንባት መታቀዱን አንስተዋል።

ልማት ጽሕፈት ቤቱ ከትምህርት እና ጤና ተቋማት ግንባታ በተጨማሪ ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ከ4 ሺህ በላይ ወጣቶችን የሥራ እድል ተጠቃሚ ለማድረግም እየሠራ መኾኑ ተገልጿል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የተጀመረው ጉዞ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ አደም ፋራህ ገለጹ።
Next articleልጆች ክረምቱን እንዴት ያሳልፉ?