የምዕራብ ጎንደር ዞንን የልማት ቀጣና ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ ነው።

10

ገንዳውኃ: ሐምሌ 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የክልል፣ የዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች እና የሀገር መከላከያ ሠራዊት መሪዎች በምዕራብ ጎንደር ዞን በገንዳ ውኃ ከተማ እየተሠሩ ያሉ የመሠረተ ልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

የሥራ ኀላፊዎቹ የእንስሳት ኳራንታይን፣ የተጀመሩ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን፣ ሙያና ቴክኒክ ኮሌጅ እና የኢንዱስትሪ መንደሮች ጎብኝተዋል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ እንዳለው ማሩ በሚሠሩ የልማት ሥራዎች ማኅበረሰቡ ተሳትፎውን እና ድጋፍን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል። አካባቢውን ሰላም እያደረግን ኅብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚ ማድረግ ያስፈልጋል ነው ያሉት።

የአማራ ክልል የሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ዓባይነህ ጌጡ ተጀምረው የተቋረጡ መሠረተ ልማቶች እና ወደ ሥራ ያልገቡ ፕሮጀክቶች እንዲገቡ ድጋፍ እና ክትትል እናደርጋለን ብለዋል።

የአማራ ክልል ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኀላፊ አየለ አናውጤ (ዶ.ር) ማኅበረሰቡ የእንስሳት ኳራታይኑን ከማንኛውም ጉዳት ከሚያደርስ ነገር መጠበቅ እንዳለበት ተናግረዋል።

ሙያና ቴክኒክ ኮሌጁ ሚያስፈልገውን የግብዓት ቁሳቁስ እና የተማሪዎችን ቁጥር ከፍ ማድረግ ከቻለ ወደ ፖሊ ቴክኒክ ከፍ እንደሚል አስገንዝበዋል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ እያሱ ይላቅ ባለሀብቶች ወደ ሥራ ገብተው እንዲያለሙ ምቹ ሁኔታዎችን እንፈጥራለን ብለዋል። ዞኑን የልማት ቀጣና ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ እንደኾንም ተናግረዋል። ተጀምረው ያላለቁ ትምህርት ቤቶች ግንባታቸው አልቆ ሥራ እንዲጀምሩ ለማድረግ እየተሠራ መኾኑንም ተናግረዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleደም መለገስ ክቡር የኾነውን የሰው ሕይወት መታደግ ነው።
Next articleበየዓመቱ ችግኝ በመተከሉ የዛሮታ ወንዝ እየጠነከረ መጥቷል።