ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ጎጃም ዞን አሥተዳደር የተለያዩ ወረዳ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን በንቃት በመጠበቃቸው ሰላም ማስፈን መቻላቸውን ተናግረዋል።
አስተያዬታቸውን ለአሚኮ የሰጡት የባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ ቅንባባ ከተማ ወይበይ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር አያሌው አሞኘ በጠራራ ፀሐይ ሳይቀር ስርቆት፣ እገታ እና ዝርፊያ ያስቸግራቸው እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
ለአብነትም እርሳቸው እና ቤተሰቦቻቸው ለሰርግ በወጡበት በአንዱ ቀን ቤት ለመሥራት ቆርጠው የከዘኑትን የባሕር ዛፍ አጠና ሳይቀር በቀን በሌቦች እንደተወሰደባቸው ነው የተናገሩት።
ይህም በአካባቢው ይፈጸም የነበረው ዘረፋ ምን ያህል የተደራጀ እና የከፋ እንደነበር ያሳያል ብለዋል።
በሰላም እጦት ያማረሩት የቀበሌው ነዋሪዎችም በጉዳዩ ዙሪያ መክረው እና ዘክረው በየጎጡ በመደራጀት አካባቢያቸውን ለመጠበቅ መወሰናቸውን አውስተዋል።
ቃልን በተግባር በመፈጸማቸውም ዛሬ ላይ ስርቆት እና ዝርፊያን ማስቀረት መቻላቸውን ነው አቶ አያሌው የገለጹት።
ሌላው በሰሜን አቸፈር ወረዳ ሊበን ከተማ የችሀ ቀበሌ ነዋሪ አስረስ ረታ በሌቦች በመማረራቸው “የአካባቢያችን ሰላም ራሳችን መጠበቅ ካልቻልን ማን ይጠብቅልናል?” በሚል ቀና መንፈስ ወደ ተጨባጭ ሥራ መግባታቸውን ተናግረዋል።
ቀደም ሲል በቀበሌው አይደለም ሌሊት ቀንም ጭምር ስርቆት ነዋሪውን ማኀበረሰብ አስመርሮት ነበር ነው ያሉት።
በተለይ ሴት ልጅ ብቻዋን ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ የማትችልበት ደረጃ ላይ መደረሱ የኹኔታውን አስቸጋሪነት ይጠቁማል ነው ያሉት።
በመኾኑም ሀገሬው ተነጋግሮ አካባቢውን በየተራ በመጠበቁ አኹን ላይ ሰላምን በማስፈን ስርቆትን መግታት መቻሉን አርሶ አደር አስረስ ጠቁመዋል።
የይነሳ ቀበሌ ነዋሪው አርሶ አደር በቀለ አቲገኝ ደግሞ በአካባቢያቸው ሕጻናት ሳይቀሩ ተሰረቀው እየተወሰዱ ከፍተኛ ገንዘብ ይጠየቅባቸው እንደ ነበር ነው የተናገሩት።
ይኹን እና መንግሥት የፈጠረላቸው የግንዛቤ ስርጸት እና ድጋፍን በመጠቀም አካባቢያቸውን ”በጓድ” እየተደራጁ ቀን እና ሌሊት መጠበቅ ከጀመሩ ጀምሮ ብዙ ነገሮች ተቀይረዋል።
“ሰው የድረሱልኝ ጥሪ ሲያሰማ ፈጥኖ ምላሽ የሚሰጠው ቁጥር ከፍተኛ ኾኗል፤ ሰላምም ሰፍኗል” ብለዋል።
የባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ ሰላም እና ጸጥታ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ዋና ኢንስፔክተር አሰፋ ወንድምአገኝ ለአርሶ አደሮች አደረጃጀት ስለተፈጠረላቸው አካባቢያቸውን መጠበቅ ችለዋል፡፡
በመኾኑም ሰው በሰላም ወጥቶ በሰላም መግባት እና ሃብት ንብረቱ እንዲጠበቅ ማድረግ ተችሏል ነው ያሉት፡፡ ይህንን ጅማሮም ለማስቀጠል እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡
በኀብረተሰቡ የነቃ ጥበቃ አካባቢውን ሰላም ማድረግ ተችሏል።
የሰሜን ጎጃም ዞን አሥተዳደር ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ገብረሥላሴ ታዘብ በየአካባቢው ስርቆት፣ ዘረፋ እና እገታ የመበራከቱ ምክንያት ጫካ የገባው ኀይል በፈጠረው ምስቅልቅል በመጣ ሥርዓት አልበኝነት እንደ ነበር አስታውሰዋል።
ይኹንና በጥምር የጸጥታ ኀይሉ እና በኀብረተሰቡ የተቀናጀ ጠንካራ ሥራ በዞኑ ሙሉ በሙሉ መንግሥታዊ መዋቅር ሥራላይ ይገኛል ብለዋል።
የዞኑን ማኅበረሰብም በሰላም እና ደህንነት ዙሪያ በማወያየት እና በየአካባቢያቸው አደረጃጀቶችን በመፍጠር በንቃት እንዲጠብቁ በመሠራቱ አዎንታዊ ለውጥ መጥቷል ብለዋል። ዘረፋ፣ ቅሚያ እና እገታ እንዲቆም ተደርጓልም ነው ያሉት።
ማኅበረሰቡም ባገኘው ሰላም ወጥቶ በሰላም ከመግባት ባለፈ ልማቱን በሙሉ አቅሙ እያከናወነ እንደሚገኝ ነው መምሪያ ኀላፊው ያብራሩት፡፡
ሰላምን መጠበቅ ለጸጥታ ኀይሉ ብቻ የሚተው ጉዳይ አይደለም ያሉት አቶ ገብረሥላሴ ከፍተኛ ዋጋ ተከፍሎ የተገኘው ሰላም በዘላቂነት ጸንቶ እንዲዘልቅ ሁሉም አካባቢውን በመጠበቅ ረገድ የበኩሉን ሚና ማበርከት አለበት ብለዋል፡፡
በሙሉጌታ ሙጨ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን