
ደብረ ማርቆስ: ሐምሌ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በ2017 በጀት ዓመት ባለሀብቶች ወደ ከተማዋ ገብተው እንዲያለሙ በተሠራው ሥራ ከ6 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 108 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠት መቻሉን የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳድር አሥተዳደር አስታውቋል።
የደብረማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኀላፊ ተመስገን ተድላ ከተማዋን ለአልሚ ባለሀብቶች ምቹ ለማድረግ እና በኢንዱስትሪ ፖርኮች መሰረተ ልማት ለማሟላት ከአጋር አካላት ጋር በቅንጅት በመሠራቱ አልሚ ባለሀብቶች ካለፉት ዓመታት በተሻለ ወደ ከተማዋ መምጣታቸውን ገልጸዋል።
ወደ ምርት ለገቡ ባለሀብቶች የገበያ ትስስር ለመፍጠር ጥረት ተደርጓል ያሉት ኀላፊው ለ25 አልሚ ባለሀብቶች ከ193 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር ተጠቃሚ እንዲኾኑ ማድረግ ተችሏል ብለዋል። በከተማዋ የሚገኙ ባለሀብቶች በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ እንዲሰማሩ በተሠራው የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ 130 የሚኾኑ ባለሀብቶች ወደ ዘርፉ ለመግባት በሂደት ላይ መኾናቸውንም ተናግረዋል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮችን የመሰረተ ልማት በማሟላት ከተማዋን ለኢንቨስትመንት ምቹ ለማድረግ እየተሠራ መኾኑንም ገልጸዋል። በደብረ ማርቆስ ከተማ ከ900 ሄክታር በላይ መሬት ለኢንቨስትመንት ምቹ በማድረግ ወደ ከተማዋ ለሚመጡ አልሚዎች ለማስተላለፍ እየሠሩ መኾናቸውንም አመላክተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!