
ደብረ ማርቆስ: ሐምሌ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በዞኑ በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት ከ900 በላይ ኪሎ ሜትር ነባር መንገድ መጠገን ተችሏል። 88 ኪሎ ሜትር መንገድ በአዲስ ፣9 ከፍተኛ እና መለስተኛ ድልድዮች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት መኾናቸውን የዞኑ መንገድ መምሪያ ኀላፊ ማናየ አዳነ ተናግረዋል። ለመንገድ ጥገና እና ለድልድዮች ግንባታ ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ሀብት በማሰባሰብ ወደ ሥራ መገባቱን አስታውቀዋል።
በጸጥታው ችግር ውስጥም ኾኖ የኅብረተሰቡን የመንገድ መሠረተ ልማት ጥያቄ ለመመለስ ጥረት ተደርጓልም ብለዋል። በፌደራል ደረጃ የሚገነቡ የአስፋልት መንገድ ፕሮጀክቶችም በጸጥታ ችግሩ የሚፈለገውን ያክል እቅድ ማሳካት ባይቻልም ከማኅበረሰቡ ጋር በመነጋገር የተጀመሩ መንገዶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ክትትል እየተደረገ መኾኑን ገልጸዋል።
የተገነቡ ተቋማት ዘላቂ ጥቅም እንዲሰጡ ኅብረተሰቡ በባለቤትነት መንከባከብ ይገባዋል ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!