የተተከሉ ችግኞች እንዲጸድቁ ክትትል እንደሚደረግ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይ ተናገሩ።

16

አዲስ አበባ: ሐምሌ 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በየካ ክፍለ ከተማ በወረዳ 2 ጉራራ አካባቢ “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ መልዕክት የ7ኛ ዙር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሂዷል።

በመርሐ ግብሩም የቢሮው የሥራ ኀላፊዎች እና ሠራተኞች ተገኝተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኀላፊ ጃንጥራር ዓባይ በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ተቋሙ ከ2 ሺህ በላይ ችግኞች ተተክተዋል ብለዋል። የተተከሉ ችግኞችን እንዲጸድቁም ክትትል ይደረግላቸዋል ነው ያሉት።

የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብርሃኑ ረታ
በየካ ክፍለ ከተማ ትልቁ የጫካ ፕሮጀክት መገኛ መኾኑን ታሳቢ በማድረግ በአካባቢው የሚተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ የተዋቡ እንዲኾኑ እንሠራለን ብለዋል።

የችግኝ ተከላው ተሳታፊዎችም መትከል ብቻ ሳይኾን የተተከሉት እንዲጸድቁ እንደሚሠሩ ተናግረዋል።

በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በመላው ሀገሪቱ ከ7 ነጥብ 5 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን ለመትከል ሥራ መጀመሩ ይታወሳል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleዓባይ ባንክ የደንበኞችን ፍላጎት ለማርካት እና የማኅበራዊ ኀላፊነቱን ለመወጣት እየሠራ መኾኑን ገለጸ።
Next articleየኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በ2018 በጀት ዓመት የደንበኞችን ርካታ ለማረጋገጥ ይሠራል።