ዑስታዝ አቡበከር አህመድ ለሁለተኛ ጊዜ የዕለት ፍጆታና የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ፡፡

298

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 26/2012 ዓ.ም (አብመድ) ዑስታዝ አቡበከር አሕመድ ለበደቡብ ወሎ ዞን እና ደሴ ከተማ አስተዳደር የኮሮና ቫይረስ ተፅዕኖን ለመቀነስ የሚረዳ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ የዕለት ፈጆታ ምግብና የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ድጋፉ በዑስታዝ አቡበከር አህመድ በኩል ሲደረግ የዛሬው ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡ ከተማ አስተዳደሩና ዞኑ የተደረገው ድጋፍ ሌሎችን የሚያነሳሳ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የኮሮና ቨይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖዎችን እያሳረፈ ይገኛል፡፡ በዚህ ወቅት የማኅበረሰቡና የበጎ አድራጊዎች የግልና የቡድን መረዳዳቶች የሕይወትን ተስፋ ለነገ በማሻገር ትልቅ አስተዋጽኦ አለው፡፡

ዑስታዝ አቡበከር አህመድ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ለዜጎች ድጋፍ ከሚያርጉ በጎ አድራጊዎች መካከል ናቸው፡፡ ከዚህ በፊት ደሴ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ በደቡብ ወሎ ዞን ለሚገኙ ችግረኞች የዕለት የምግብ ፍጆታ የሚውል ድጋፍ በተወካያቸው አማካኝነት አስረክበው ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ በአካል በመገኘት ለደሴና ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደሮችና ለደቡብ ወሎ ዞን አንድ ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ለሁለት ሺህ ሰዎች ዱቀት፣ ዘይትና ሩዝ ለሕክምና ሙያተኞች የሚያገለግል የኬሚካል መርጫ መሣሪያ፣ ልብስ፣ ቦቲ ጫማና የሙቀት መለኪያ አስረክበዋል፡፡

‘‘ያለሃይማኖት፣ ፖለቲካና አካባቢያዊ ልዩነት የተቸገሩ ዜጎችን የምንታደግበት ወቅት ነው’’ ያሉት ዑስታዝ አቡበከር ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልጸዋል፡፡

ዑስታዝ አቡበከር ያከናወኑት በጎ ተግባር ለሌሎች ትልቅ ትምህርትና መልእክት መሆኑን የተናገሩት የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሰይድ መሐመድ የኢኮኖሚ ተፅዕኖውን ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት ከ26 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን ተናግረዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ደጀን አምባቸው -ከደሴ

ተጨማሪ መረጃዎችን
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዩቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡፡

Previous articleርእሰ መሥተዳደሩ የውኃ መስመሮች እንዳይዘረጉ በሚያደርጉ ግለሰቦች ላይ ከተማ አስተዳደሩ ጠንከር ያለ ርምጃ እንዲወስድ አሳሰቡ፡፡
Next article“ደቡብ ሱዳን ለግብጽ የጦር ሰፈር መገንቢያ ቦታ ፈቀደች” ተብሎ የተሰራጨው ዘገባ ሀሰት መሆኑን ደቡብ ሱዳን አስታወቀች።