ለመጭው ትውልድ ነጻነትን እንጂ ተሻጋሪ ዕዳ አናወርስም።

28

ሁመራ፡ ሐምሌ 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የወሰንና ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ራሱን ከህውሓት አፈና በጀግንነት የተከላከለበትን እና ለዛሬው ነጻነት ምክንያት መኾኑን በማሰብ በሁመራ ከተማ በደመቀ ኹኔታ እየተከበረ ነው።

በዓሉ “ለመጭው ትውልድ ነጻነትን እንጂ ተሻጋሪ ዕዳ አናወርስም” በሚል መሪ መልዕክት ነው እየተከበረ የሚገኘው።

ለ9ኛ ጊዜ በሚከበረው በዓል ላይ የአማራ ክልል እና የዞኑ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አዛዦች፣ ከመላው አማራ ክልል በክብር የተጋበዙ እንግዶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየደብረ ታቦር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።
Next articleጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች እና ሕጻናት አገልግሎት የሚሰጡ የሕክምና ክፍሎች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት ኾኑ።