የተፈጠሩ የፀጥታ ስጋቶችን በመቀልበስ በሕዝብ ላይ ሊደርስ የሚችለውን ምስቅልቅል መቅረፍ ተችሏል።

17

እንጅባራ፡ ሐምሌ 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በብልፅግና ፓርቲ የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ቅርንጫፍ ጽሕፍት ቤት የ2017 በጀት ዓመት የድርጅትና የፖለቲካ ሥራዎች ግምገማ በእንጅባራ ከተማ አካሂዷል።

የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አስተዳደሪ ቴወድሮስ እንዳለው በዚህ ወቅት እንደተናገሩት ብልፅግና ላለፉት ሁለት ዓመታት የተፈጠሩ የፀጥታ ስጋቶችን በመቀልበስ በሕዝብ ላይ ሊደርስ የሚችለውን ምስቅልቅል መቅረፍ የቻለ ፓርቲ ነው ብለዋል።

የፓርቲውን ስኬቶች ለማስቀጠልና ካጋጠሙ ፈተናዎች በፅናት ለመሻገር የፓርቲው አመራሮችና አባላት የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ወሳኝ መሆኑንም አንስተዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ቅርንጫፍ ጽሕፍት ቤት ኀላፊ አለሙ ሰውነት ብልፅግና በሀሳብ ልዕልና የሚያምን፣ ፅንፈኝነት እና ዋልታ ረገጥነት አጥፊ መሆናቸውን የተረዳ አካታች ኅብረ ብሔራዊ ፓርቲ መሆኑን ተናግረዋል።

ፓርቲው በበጀት ዓመቱ በየደረጃው ጠንካራ አደረጃጀቶችን በመፍጠር በርካታ ስኬታማ የድርጅትና የፓለቲካ ሥራዎችን አከናውኗልም ነው ያሉት።

በበጀት ዓመቱ የተስተዋሉ ውስንነቶችን ለማረም በቀሪ ወራት ርብርብ እንደሚደረግም ኀላፊው አስገንዝበዋል።

በመድረኩ የተገኙት በቢሮ ኀላፊ ደረጃ የአማራ ክልል ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ አማካሪ ሽቤ ክንዴ ብልፅግና ፓርቲ በፈተናዎች ውስጥ ሆኖ በርካታ ስኬቶችን ያስመዘገበ ፓርቲ መሆኑን ተናግረዋል።

በፓርቲው አመራሮች ቁርጠኝነት ለፍፃሜ የበቁ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ፣ አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎች ልማትና እድሳት እንዲሁም አካታች የፖለቲካ ምህዳር መዘርጋትና ሌሎችንም በአዎንታ አንስተዋል።

ያለ ጠንካራ ፓርቲ ጠንካራ መንግሥትም ሆነ ጠንካራ ሀገር እውን ሊሆን አይችልም ያሉት አማካሪው የፓርቲውን ጥንካሬ ለማዝለቅ የአመራሩና የአባላት ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑንም ገልጸዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበደብረ ማርቆስ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውኃን ተደራሽነት ለማሳደግ እየተሠራ ነው።
Next articleበአዲስ አበባ ውጤታማ ሥራዎች መሠራታቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።