
ባንኩ ለ100 የኢትዮጵያ ብር 57 ነጥብ 5872 ሩብል ወይም ለ1 ብር 0 ነጥብ 575872 ሩብል የምንዛሬ ተመን አስቀምጧል።
ባንኩ ለኢትዮጵያ ብር ምንዛሬ ተመን የኮድ ቁጥር 230 የሰጠ ሲሆን በየዕለቱም የምንዛሬ ተመኑን የሚያሳውቅ ይሆናል።
የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ የኢትዮጵያን ብር ጨምሮ የ12 ሀገራት ገንዘቦች ከሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ ጋር ያላቸውን ይፋዊ የምንዛሪ ተመን ለማስቀመጥ ውሳኔ ላይ መድረሱን ከቀናት በፊት ይፋ አድርጎ ነበር።