በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ውጤታማ ሥራዎች ተሠርተዋል።

8

ሰቆጣ፡ ሐምሌ 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር በቀጣይ 90 ቀናት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥ ዙርያ የሚሠሩ ተግባራት የዕቅድ ትውውቅ የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በክረምቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከበጋው የተሻለ ለመሥራት መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል።

የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ጤና መምሪያ ኀላፊ አሰፋ ነጋሽ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ ኩፍኝ፣ ትክትክ ሳል፣ የአተት እና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል የተሠራው ሥራ ውጤታማ መኾኑን ገልጸዋል።

በዋግ ባሉ ቆላማ ወረዳዎች የተከሰተውን የወባ ወረርሽኝ ለመከላከል ከ300ሺህ በላይ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ያሳተፈ “የጠንካራ አርብ እጆች ወባን መከላከል” በሚል መርህ የተሻለ ሥራ መሠራቱን አንስተዋል።

በአካባቢው የጸጥታ ችግር ባሉባቸው አካባቢዎች የጤና ተቋማትን ወደ ሥራ በማስገባት ከ10ሺህ በላይ እናቶች በጤና ተቋማት እንዲወልዱ ተደርጓል ነው ያሉት።

በበጋው ተግባር የማኅበረሰቡን ጤንነት ለመጠበቅ የተሠራው ተግባር ውጤታማ እንደነበረ የገለጹት ኀላፊው በቀጣዩ የ90 ቀናት በክረምቱ የሚከሰቱ ወረርሽኞችን በመለየት የቅድመ መከላከል ተግባራት ላይ ትኩረት እንደሚያደርጉ ጠቁመዋል።

የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ ግብርና መምሪያ ኀላፊ አዲሱ ወልዴ በበጋው የተቀናጀ የልማት ተግባር በበጋ መስኖ ልማት የተሻለ አፈጻጸም እንደነበራቸው ተናግረዋል።

የተቀናጀ የተፈጥሮ ሃብት ሥራም ከ369 በላይ ተፋሰሶችን ከ100ሺህ በላይ የማኅበረሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ የአፈር እቀባ ሥራ መሠራቱን ገልጸዋል።

በተለይም በመስኖ ልማት በሽንኩርት እና በማንጎ ተክሎች የተገኘው ውጤት ከዞኑ ገበያ አልፎ እስከ አጎራባች ክልሎች ማቅረብ እንደተቻለ ገልጸዋል።

በዚህም ከ700ሺህ ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱን ነው የገለጹት።

በቀጣዩ የ90 ቀናትም በክላስተር እና በኩታ ገጠም የተመረጡ ዘሮችን ለመዝራት ተዘጋጅተናል ያሉት ኀላፊው በአረንጓዴ አሻራም ከ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ለመትከል አቅደው እየሠሩ መኮናቸውን ተናግረዋል።

በንቅናቄ መድረኩም በቀጣይ 90 ቀናት የሚሠሩ የትኩረት ነጥቦች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸል። ሐምሌ 4/2017 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት ተለይተው ወደ ተግባር ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ዘጋቢ፦ ደጀን ታምሩ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየጤና ጣቢያዎችን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማስተካከል እየተሠራ ነው።
Next articleየኢትዮጵያ ብር በሩሲያ የባንክ ምንዛሬ ውስጥ ተካተተ። የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ የኢትዮጵያን ብር በምንዛሬ ዝርዝር ውስጥ አካቷል።