
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 25/2012 ዓ.ም (አብመድ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ለ3 ሺህ 932 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በ87 ሰዎች ላይ የኮሮናቫይረስ እንደተገኘ ጤና ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል፤ ሁለት ሰዎች ሕይወታቸው ካለፈ በኋላ በተደረገ የአስከሬን ምርመራ ቫይረሱ እንደነበረባቸው ተረጋግጧል፡፡
ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ከ10 እስከ 70 ዓመት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ አዲስ በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡ 87 ሰዎች መካከል 41 የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክም ሆነ አስቀድሞ በሕክምና ከተረጋገጠ ታማሚ ጋር ንክኪ የላቸውም፡፡ 28 የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ነበራቸው፤ 18 ደግሞ በበሽታው መያዙ አስቀድሞ በሕክምና ከተረጋገጠ ሰው ጋር ንክኪ አላቸው ተብሏል፡፡
ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 67 ሰዎች ከአዲስ አበባ ናቸው፤ ቀሪዎቹ ሰባት ከአማራ፣ ስድስት ከኦሮሚያ፣ አራት ከሶማሌ፣ ሁለት ከትግራይ እና አንድ ከሐረሪ ክልሎች ናቸው፡፡
ትናንት ስምንት ሰዎች ከሶማሌ እና ስድስት ሰዎች ከኦሮሚያ ክልሎች ከቫይረሱ ማገገማቸውንም የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በኢትዮጵያ እስከዛሬ ድረስ 116 ሺህ 309 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 1 ሺህ 344 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፤ 14 ሕይወታቸው አልፏል፤ 1 ሺህ 97 ሰዎች በሕክምና ሂደት ላይ ሲሆኑ 231 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዩቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡፡
