በጎንደር ከተማ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች የነዋሪዎቹን የሥራ ባሕል መቀየር የቻሉ ናቸው።

9

ጎንደር፡ ሐምሌ 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ‎የብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊዎች የጎንደር ከተማን የኮሪደር ልማት እና የአጼ ፋሲል አብያተ መንግሥታት የቅርስ እድሳትን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ላይ የተገኙት በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ፍሰሃ ደሳለኝ ‎በጎንደር ከተማ እየተሠሩ ያሉ የልማት ሥራዎች ለኅብረተሰቡ የዘመናት የልማት ጥያቄ ምላሽ የሰጡ መኾናቸውን ገልጸዋል።

‎በከተማዋ እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች የነዋሪዎቹን የሥራ ባሕል መቀየር የቻሉ መኾናቸውን ነው የተናገሩት።

‎በብልጽግና ፓርቲ የጋምቤላ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ኢንጂ ቦጋለ (ዶ.ር) የከተማዋን ታሪካዊነት የጠበቁ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን በምልከታቸው እንዳረጋገጡ ተናግረዋል።

‎በብልጽግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ኀላፊ አየለ ተስፋ በጎንደር ከተማ እየተሠሩ ያሉ የልማት ሥራዎች የከተማዋን ውበት የጨመሩ መኾናቸውን ጠቁመዋል። ከተመለከቷቸው የልማት ሥራዎች ተሞክሮ በመውሰድ ወደመጡባቸው አካባቢዎች ለማስፋት እንደሚሠሩም ነው የገለጹ።

‎የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው ከተማዋ ለበርካታ ዓመታት ከልማት ርቃ የቆየች ቢኾንም እሁን ላይ እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች የከተማዋን ገጽታ የቀየሩ መኾናቸውን ተናግረዋል።

‎የከተማ ማስዋብ ሥራዎች ከተሠሩ በኋላ የኮንፍረንስ ቱሪዝም እንቅስቃሴም እየጨመረ እንዲመጣ ማድረጉ ተመላክቷል።

ዘጋቢ፦‎ዳንኤል ወርቄ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየአማራ ክልል የብልጽግና ጉዞ አብሳሪ ክልል ነው።
Next articleሰላም እና ልማት እንዲረጋገጥ ሴቶች ተሳትፏቸውን እንዲያጠናክሩ ተጠየቀ።