
ሰቆጣ፡ ሐምሌ 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር በሰቆጣ ከተማ “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ መልዕክት የ90 ቀናት የልማት፣ የፖለቲካ፣ የሰላም፣ የመልካም አሥተዳደር ተግባራት ዕቅድ እና የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው።
በንቅናቄ መድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያሥተላለፉት የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ ኃይሉ ግርማይ በበጋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተመዘገቡ ውጤቶችን በማጠናከር በክረምቱ የተሻለ ሥራ ለመሥራት በዕቅድ መመራት ያሥፈልጋል ብለዋል።
በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ሕዝቡ ከልማቱ ጎን እና ከመንግሥት ጎን ተሰልፎ በርካታ ውጤቶችን ማስመዝገብ እንደተቻለ አንስተዋል።
በቀጣይ 90 ቀናትም በልማት፣ በበጎ ፈቃድ እና ሰላምን በማጽናት በኩል ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ይገባል ነው ያሉት።
የዋግ መገለጫ የኾነው የሻደይ በዓል የዕቅዱ አንድ አካል በማድረግ በተሻለ መንገድ ለማክበር መዘጋጀታቸውን የጠቆሙት ዋና አሥተዳዳሪው ለዚህም ዝርዝር ተግባራትን በማስቀመጥ የጋራ ተግባር ሊደረግ እንደሚገባም አሳስበዋል።
ዘጋቢ፦ ደጀን ታምሩ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን