በኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ከ75 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተሠሩ ፕሮጀክቶችን አስመረቀ።

19

ከሚሴ፡ ሐምሌ 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ አሊ ሰይድ በ2017 በጀት ዓመት በወረዳው ከ75 ሚሊዮን ብር በላይ በኾነ ወጭ 13 ፕሮጀክቶችን በመገንባት ለአገልግሎት ክፍት ማድረግ እንደተቻለም አስረድተዋል። ከተገነቡ ፕሮጀክቶች መካከል የመስኖ ካናል ግንባታ፣ የንፁህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት፣ የመብራት እና የኔትዎርክ መሠረተ-ልማት ዝርጋታ እና ሌሎች የመሠረተ ልማቶች መኾናቸውን ተናግረዋል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ አህመድ አሊ ወረዳው ትላልቅ ፕሮጀክቶችን አቅዶ መገንባት የቻለው ሰላሙን በማረጋገጡ በመኾኑ አኹንም ሰላሙን ዘላቂ ለማድረግ ሊሠራ ይገባል ብለዋል። ከአጎራባች ወረዳዎች ጋር የጀመረውን የጋራ የሰላም ግንባታ በትብብር በመሥራት በልማት የተሳሰረ ማኅበረሰብ መፍጠር እንደሚገባውም አስረድተዋል።

የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ነዋሪዎች በበኩላቸው ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት የኾኑ ፕሮጀክቶች የማኅበረሰቡ የልማት ጥያቄዎች እንደነበሩ ጠቅሰው የወረዳውን ሕዝብ ልማት የሚያፋጥኑ ናቸው ብለዋል። የመስኖ ካናል የተገነባላቸው የወረዳው አርሶ አደሮች ከዚህ በፊት በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ያመርቱ እንደነበር ጠቅሰው አኹን ላይ የመስኖ ካናሉ በመገንባቱ በዓመት ሦስት ጊዜ ለማምረት እንደሚያስችላቸው አብራርተዋል።

ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሒም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየሚመዘበር ንብረትን በመከላከል ለልማት ማዋል እና ፍትሕን ማረጋገጥ ይገባል።
Next articleበክረምቱ የተሻለ ሥራ ለመሥራት በዕቅድ መመራት ያሥፈልጋል።