
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ክልላዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርን በሰሜን ጎጃም ዞን ይልማና ዴንሳ ወረዳ በአቦላ ተራራ አስጀምረዋል።
በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተሳትፈዋል።
“በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ መልዕክት እንደ ሀገር የተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ዘንድሮ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞች እንደሚተከሉ ይጠበቃል። አሁን ላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ለተከላ ዝግጁ መደረጋቸውም ተገልጿል።
ከተዘጋጁ ችግኞች ውስጥ የፍራፍሬ፣ ሀገር በቀል የደን ችግኞች፣ የእንስሳት መኖ እና ሌሎች የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ችግኞች ይገኙበታል። ከ205 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ ችግኞች እንደሚተከሉም ተመላክቷል።
ዘጋቢ፦ ታርቆ ክንዴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን