ርዕሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ እና የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ።

30

“ስፖርት ለአሸናፊ ሀገር” በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀውን ስለኢትዮጵያ መድረክ ምክንያት በማድረግ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ እና የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታድየም አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።

ርዕሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በባሕር ዳር ከተማ ያዘጋጀውናን ስለ ኢትዮጵያ የፎቶግራፍ አውደ ርዕይም ጎብኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያዘጋጀው ሁለተኛ ምዕራፍ ስለኢትዮጵያ መድረክ በባሕር ዳር ከተማ ስፖርት ለአሸናፊ ሀገር በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀ መድረክ ነው።

Previous article“ፍልሰት በአግባቡ ከተመራ የማደግ እና አካታች የልማት ዕድልን ይፈጥራል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Next articleየምሥራቅ ዕዝ በብርሸለቆ የውትድርና ትምህርት ቤት ለ2ኛ ዙር ያሠለጠናቸውን የዕዙ መሪዎች አስመረቀ።