
ደሴ: ሰኔ 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) ከደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ጋር በሐይቅ ከተማ እየተከናወነ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት ተመልክተዋል።
በክልሉ ከተሞች ጽዱ እና ለነዋሪዎች ምቹ እንዲኾኑ ለማድረግ እየተሠራ መኾኑን የገለጹት ምክትል ርእሰ መሥተዳደሩ በሐይቅ ከተማ የተጀመረው ሥራም አስደሳች እንደኾነ አንስተዋል።
በገበታ ለትውልድ እየለማ የሚገኘው የሎጎ ሐይቅን ጨምሮ ኅብረተሰቡን በማሳተፍ በውስጥ ገቢ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ሥራ ሲጠናቀቅ ሐይቅ ከተማ የብልጽግና ማሳያ ትኾናለች ብለዋል።
የደቡብ ውሎ ዞን ዋና አሥተዳደሪ አሊ መኮንን በዞኑ በሦሥት ከተሞች የኮሪደር ልማት ሥራ እያከናወኑ መኾኑን ገልጸዋል። በሐይቅ ከተማም እየተከናወነ ያለው እንቅስቃሴ ጅምሩ አበረታች እንደኾነ ተናግረዋል።
በሐይቅ ከተማ በ58 ሚሊዮን ብር እየተከናወነ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት ሥራ ከታኅሣሥ 2018 ዓ.ም በፊት ለማጠናቀቅ እየተሠራ መኾኑን የከተማዋ ከንቲባ ከድር ሙሃመድ ተናግረዋል።
ዘጋቢ:- ተመስገን አሰፋ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን