በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ያልተጠናቀቁ የልማት ሥራዎችን ለማጠናቀቅ እና አዳዲስ ተግባራትን ለመፈጸም እየተሠራ ነው።

5

እንጅባራ፡ ሰኔ 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የቀጣይ 90 ቀናት የክረምት ሥራዎች ዕቅድ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በእንጅባራ ከተማ ምክክር አካሂዷል።

በብልጽግና ፓርቲ የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ቅርንጫፍ ጽሕፍት ቤት ኀላፊ አለሙ ሰውነት በሚቀጥሉት 90 ቀናት በበጋ ወራት በተለያዩ ምክንያቶች ያልተጠናቀቁ ሥራዎች የሚጠናቀቁበት እና አዳዲስ ተግባራት በንቅናቄ የሚፈፀሙበት መኾኑም ነው የተናገሩት።

የሕግ ማስከበር ሥራዎችን ማጠናከር፣ የመኸር ሰብል ልማት፣ የወባ በሽታ ስርጭትን መግታት፣ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ የአረንጓዴ አሻራ እና ሌሎችም የፓርቲና የመንግሥት ተግባራት በትኩረት የሚፈጸሙ መኾናቸውን ገልጸዋል። የደረጃው የሚገኙ የመንግሥት መዋቅሮች ለዕቅዱ ተፈፃሚነት ሊተጉ እንደሚገባም ኀላፊው አስገንዝበዋል።

የምክክር መድረኩ ተሳታፊዎችም የመንግሥት እና የሕዝብ አቅሞችን አቀናጅቶ በመጠቀም የኅብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትጋት እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleአባቶች የተሰጣቸውን ጸጋ በመጠቀም ለሰላም መስፍን በትኩረት እንዲሠሩ ‎የአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ አሳሰበ።
Next articleየክልሉን አስተማማኝ ሰላም ለማረጋገጥ ሁሉም የድርሻውን መወጣት አለበት።