
ባሕር ዳር: ሰኔ 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌትናንት ጄኔራል መሐመድ ተሰማ የቀጣይ የሕግ ማስከበር ተግባራት ዙሪያ ከአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።
ሌትናንት ጄኔራል መሐመድ ተሰማ የሕዝብን ጥያቄ ሽፋን በማድረግ በክልሉ የተፈጠረው የጽንፈኝነት እንቅስቃሴ የክልሉን ሕዝብ ለከፋ ስቃይ መዳረጉን ተናግረዋል። የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና ሌሎችም የክልሉ ጥምር የጸጥታ አካላት በከፈሉት መስዋዕትነት በብዙ የክልሉ አካባቢዎች ሰላም እየሰፈነ መምጣቱንም ተናግረዋል።
የመንግሥት መዋቅሩ እና ሰላም ወዳዱ ማኅበረሰብ ለሕግ ማስከበር ሥራው ጠንካራ ደጀን እንደነበሩም አንስተዋል። የጽንፈኛው ሕልውና ለማክሰም ከሕዝብ የመነጠል እና የሃብት ምንጮችን የማምከን ሥራ እየተሠራ መኾኑንም ጠቁመዋል። በጠላት የተያዙ ቀጣናዎችን ሙሉ በሙሉ ከጸጥታ ስጋት ነጻ ለማድረግ የተጀመረው ሕግ የማስከበር ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን