ከ10 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ለተከላ ማዘጋጀቱን የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

13

ደብረ ማርቆስ: ሰኔ 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ”በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ መልዕክት የአረንጓዴ ዐሻራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሂዷል።

የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ግብርና መምሪያ ኀላፊ መለሰ ሙላት በክረምት ወቅት ከ240 ሔክታር በላይ መሬት በችግኝ ለመሸፈን እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል። ለአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብርም በቂ ዝግጅት መደረጉን አስታውቀዋል። ከዚህ በፊት የተተከሉ ችግኞችን የጽድቀት መጠን ከፍ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።

የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ተሾመ ዋለ መርሐ ግብሩ እንደ ሀገር እየተመናነመነ የመጣውን የደን ሃብት ለመመለስ እና የተፈጥሮ ሚዛንን ለማስተካከል የሚችል ሁለንተናዊ ጥቅም ያለው ነው ብለዋል። በዚህ መልካም ተግባር መሳተፍ ይጠበቃል ነው ያሉት። ችግኝ በመትከል የተሳተፉ ወጣቶች የተተከሉ ችግኞች ለተፈለገው ጥቅም እንዲውሉ እንክብካቤ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበተደጋገሚ የሚያጋጥመውን የኃይል መቆራረጥ ለመቀነስ እየሠራ መኾኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ።
Next articleየፈተና ውጤት ማስታወቂያ