
ደብረ ብርሃን: ሰኔ 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ)የአማራ ክልል ሴቶች፣ ሕጻናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በደብረ ብርሃን ከተማ እያካሄደ ነው።
የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት በከተማው እና ዙሪያው የሴቶችን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሢሠራ ቆይቷል ብለዋል፡፡ ነጋዴ ሴቶችን በማደራጀት የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ የተሠሩ ተግባራት መኖራቸውን ተናግረዋል።
የአማራ ክልል ሴቶች፣ ሕጻናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኀላፊ ዝና ጌታቸው የሴቶች፣ ሕጻናት፣ አካል ጉዳተኞች እና አረጋውያንን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በቅንጅት ሢሠራ መቆየቱን አስታውቀዋል፡፡ በበጀት ዓመቱም የእነዚህ ወገኖች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት መከናወናቸውን አብራርተዋል፡፡
ሴቶችን በተለያዩ አደረጃጀቶች በማሳተፍ ኢኮኖሚዊ ተጠቃሚነታቸውን፣ ፖለቲካዊ ተሳትፏቸውን እና የውሳኔ ሰጪነት አቅማቸውን ለማሳደግ የተከናወኑ ሥራዎች መኖራቸውን ገልጸዋል። በማኅበራዊ ጥበቃ ዘርፍ፣ በከተሞችም ኾነ በገጠር አካባቢዎች በሚከናወኑ የልማታዊ የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ሥራዎች ሴቶች እንዲካተቱ መደረጉን ጠቁመዋል፡፡
ዘጋቢ:- ገንዘብ ታደሰ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
