
ባሕርዳር፡ ሰኔ 27/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ”ሰላም ለሁሉም፣ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ መልዕክት በምሥራቅ ጎጃም ዞን በአዋበል ወረዳ የወጀል ከተማ ነዋሪዎች ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እያካሄዱ ነው።
በሰላማዊ ሰልፉ ሰላሜን እጠብቃለሁ ብልጽግናየን አረጋግጣለሁ፣ ሰላምን እንሻለን፣ ክልላችንን የሰላም እና የልማት ማዕከል ለማድረግ ሁላችንም ለሰላም ዘብ እንቆማለን፣ ጽንፈኝነትን እናወግዛለን፣ ከመንግሥት ጎን እንቆማለን፣ መንግሥት ሕግን በማስከበር የዜጎችን ሰላም ሊያስጠብቅ ይገባል የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶች እየተላለፉ ይገኛሉ። ከምሥራቅ ጎጃም ዞን ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው መንግሥት እየወሰደ ያለውን እርምጃ እንደሚደግፉም ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን