ዘላቂ ሰላምን ለማጽናት እና የልማት እንቅስቃሴዎችን ለማጠናከር ዓላማ ያደረገ ውይይት ከወረኢሉ ከተማ እና ወረዳ ነዋሪዎች ጋር እየተካሄደ ነው።

10

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) ከወረኢሉ ከተማ እና ወረዳ ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር በወቅታዊ የሰላም እና የልማት ጉዳዮች ላይ ውይይት እያካሄዱ ይገኛሉ።

“ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ መልዕክት ነው ውይይቱ እየተካሄደ የሚገኘው። በውይይቱ የአማራ ክልል ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ ኀላፊ ኃይሌ አበበ፣ የደቡብ ወሎ ዞን አሥተዳዳሪ አሊ መኮንን፣ በብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ወሎ ዞን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋ ዳኛው፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች እና ሌሎች የማኅበረሰብ ተወካዮች ተሳትፈዋል። ውይይቱ ዘላቂ ሰላምን ለማጽናት እና የልማት እንቅስቃሴዎችን ለማጠናከር ዓላማ ያደረገ ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየፈተና ውጤት ማስታወቂያ
Next articleክልሉን የልማት ማዕከል ለማድረግ ለሰላም እንደሚቆሙ በአዋበል ወረዳ የወጀል ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።