“ሪፎርሙ የፋይናንስ ሴክተሩን አነቃቅቷል”

4

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ.ር)

ባሕር ዳር: ሰኔ 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ.ር) ከምክር ቤት አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል። የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በፋይናንስ ሴክተሩ ላይ መነቃቃት ማምጣቱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ከዚህ ውስጥ ደግሞ በዚህ ዓመት የብድር አገልግሎቱ ከባለፈው ዓመት በ75 በመቶ መጨመሩን ገልጸዋል። ከዚህ ውስጥ የግል ሴክተሩ 80 በመቶ ድርሻ እንዳላቸው ገልጸዋል። በተሠራው ሪፎርም የፋይናንስ ሴክተሩን ከነበረባቸው እዳ ማዳን መቻሉን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስቱሩ እንዳብራሩት የሞባይል ተጠቃሚው 55 ሚሊዮን ደርሷል፤ የዲጂታል የገንዘብ ልውውጡ 12 ነጥብ 5 ትሪሊዮን ኾኗል። ይህም የዲጂታል የገንዘብ ልውውጥ ድርሻ ከካሽ የገንዘብ ልውውጥ የበላይነቱን መውሰዱን ገልጸዋል።

11 ሚሊዮን የሚኾኑ ወጣቶች በስልክ ብቻ የ24 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ብድር ተጠቃሚ ኾነዋል። ይህም የብድር ሥርጭቱ ከጥቂት ሰዎች ወደ ብዙ ሰዎች እንዲደርስ አድርጓል ብለዋል። በዚህ ዓመት 5 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ኤክስፖርት ለማድረግ ታቅዶ እስከ አሁን 8 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ማሳካት ተችሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ወደ ሀገር ውስጥ ከሚገባ የውጭ ምንዛሬ (ረሚታንስ) 7 ቢሊዮን ዶላር፣ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት 4 ቢሊዮን ዶላር ተመዝግቧል፣ ከሰርቪስ የተገኘው ኤክስፖርት ደግሞ 8 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ነው።

ባለፈው ዓመት ከሁሉም የውጭ ምንዛሬ ማግኛ ምንጮች የተገኘው አጠቃላይ ሃብት 24 ቢሊዮን ዶላር ሲኾን በዚህ ዓመት ወደ 32 ቢሊዮን ዶላር ማደጉን ገልጸዋል። በወጭ እና ገቢ ንግድ መካከል ይታይ የነበረውን ጉድለት በ4 ቢሊዮን ዶላር መሻሻሉን ገልጸዋል።ለኢምፖርት 19 ቢሊዮን ብር ወጭ ተደርጓል። ከዚህ ውስጥ ደግሞ ካፒታል ምርቶች ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዝ ነው ያነሱት። በዚህ ዓመት 92 ቢሊዮን ብር እዳ መከፈሉንም ገልጸዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleኢትዮጵያ በጋራ የመልማት አቋሟ እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ተናገሩ።
Next article“እስከ ነሐሴ 2017 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ ከ20 ሺህ በላይ ፕሮጄክቶች ይመረቃሉ” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)