ኢትዮጵያ በጋራ የመልማት አቋሟ እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ተናገሩ።

11

ባሕር ዳር: ሰኔ 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሠጡ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው ሕዳሴ ተጠናቅቋል፤ ክረምቱ ሲያልቅ ይመረቃል ብለዋል። ሕዳሴ እንዳይመረቅ የሚፈልጉ ኃይሎች አሉ ነገር ግን ሕዳሴን እንዳይመረቅ የሚያደርግ ነገር የለም ነው ያሉት።

ሕዳሴ ለሱዳን እና ለግብጽ በረከት ነው፣ የሚያመጣው ጉዳት የለም፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ልማት ለሁሉም ለጎረቤቶቻችን የሚጠቅም ነው ብለዋል። በሕዳሴ ግድብ ምክንያት የግብጹ አስዋን ግድብ ውኃ አለመቀነሱን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በጋራ የመልማት አቋሟም እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።

አትሥሩ አይበሉን እንጂ ለመወያየት እና አብሮ ለመሥራት ኢትዮጵያ ዝግጁ ናት ብለዋል። ሕዳሴን ስናስመርቅ የደስታችን ተካፋይ እንዲኾኑ ግብዣ አቀርብላቸዋለሁ ነው ያሉት። ለጋራ ልማት በጋራ መሥራት እንደሚገባም ተናግረዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“1 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር የሚጠይቁ የመንገድ ፕሮጀክቶች እየተሠሩ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next article“ሪፎርሙ የፋይናንስ ሴክተሩን አነቃቅቷል”