“1 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር የሚጠይቁ የመንገድ ፕሮጀክቶች እየተሠሩ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

25

ባሕር ዳር: ሰኔ 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሠጡ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው የኢትዮጵያ የመንገድ ሽፋን 175 ሺህ ኪሎ ሜትር መድረሱን ተናግረዋል። 1 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር የሚጠይቁ 300 ፕሮጀክቶች መጽደቃቸውን እና ሥራ መጀመራቸውን ገልጸዋል። 169 ፕሮጀክቶች አሁን ላይ እየተገነቡ መኾናቸውን አመላክተዋል።

ከ1 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ መንገድ በዚህ ዓመት እንደሚመረቅም አመላክተዋል። 145 ፕሮጀክቶች የመንገድ ጥገና እንዳለም ገልጸዋል። የመንገድ ፕሮጀክቶች ላይ ሰላም፣ የካሳ ክፍያ እና የተቋራጭ አቅም ችግር እንዳለም አመላክተዋል።ችግሮችን እየፈቱ መሥራት እንደሚጠበቅም አንስተዋል። ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀዳሚ የኾነ የኢንቨስትመንት ሥራዎችን እየሠራች መኾኑንም ተናግረዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleበዓመቱ 1 ነጥብ 3 ሚሊየን የውጭ ሀገር ቱሪስቶች ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል።
Next articleኢትዮጵያ በጋራ የመልማት አቋሟ እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ተናገሩ።