በዓመቱ 1 ነጥብ 3 ሚሊየን የውጭ ሀገር ቱሪስቶች ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል።

8

ባሕር ዳር: ሰኔ 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በዚህ ዓመት ብቻ ኢትዮጵያ ከ150 በላይ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶችን ማካሄዷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ገልጸዋል። 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን የውጭ ሀገር ቱሪስቶች ኢትዮጵያን መጎብኘታቸውንም ጠቅሰዋል። ይህ ቁጥር ከዚህ በፊት ከነበረው የላቀ ነው ብለዋል።

የሀገሪቱ የኢሚግሬሽን የለውጥ ሥራዎች፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥራ፣ የሆቴሎች አገልግሎት አሰጣጥ መሻሻል፣ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች መሥፋፋት እና የኮሪደር ልማት የውጭ ሀገር ጎብኝዎችን ለመሳብ ምክንያቶች እንደነበሩም ዘርዝረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የተገነቡት አንድነት ፓርክ፣ ፍሬንድ ሽፕ ፓርክ፣ ሳይንስ ሙዚየም እና ብሔራዊ ቤተ መንግሥት ብቻ ከተሠሩ ጀምሮ በ13 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሕዝብ ተጎብኝተዋል። በዚህ ዓመት ብቻ በ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሰዎች ተጎብኝተዋል ብለዋል።

በዓመቱም ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ አንዱ የሀገሪቱ ቱሪዝም እድገት ምክንያት ስለመኾኑም አንስተዋል። አየር መንገዱ በዚህ ዓመት ብቻ 13 ተጨማሪ አውሮፕላኖችን በመግዛት የአውሮፕላን ቁጥሩን ወደ 180 ማሳደጉን ተናግረዋል።

ስድስት አዳዲስ መዳረሻዎችን በመጨመር በዓለም ላይ 136 አጠቃላይ መዳረሻዎችን አበጅቷል ነው ያሉት። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አየር መንገዱ በዓመቱ ከ19 ሚሊየን በላይ ሰዎችን አጓጉዟል ነው ያሉት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“1 ነጥብ 5 ቢሊየን ኩንታል ምርት መሠብሠብ ተችሏል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next article“1 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር የሚጠይቁ የመንገድ ፕሮጀክቶች እየተሠሩ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)