የሰላም ግንባታ ጥረቶችን እና የልማት እንቅስቃሴዎችን ለማጠናከር ያለመ ምክክር በወግዲ ወረዳ ተካሄደ።

11

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) በወግዲ ወረዳ ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር በወቅታዊ የሰላም እና የልማት ጉዳዮች ላይ ምክክር አካሂደዋል። ምክክሩ “ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ መልዕክት ነው የተካሄደው።

በምክክሩ የደቡብ ወሎ ዞን አሥተዳዳሪ አሊ መኮንን፣ የብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ወሎ ዞን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋ ዳኛው፣ የልዩ ዘመቻዎች የ105ኛ ኮማንዶ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ሞሲሳ ቶላሳ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች እና ሌሎች የማኅበረሰብ ተወካዮች ተሳትፈዋል። ምክክሩ በክልሉ የሰላም ግንባታ ጥረቶችን እና የልማት እንቅስቃሴዎችን ለማጠናከር ያለመ ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleኢትዮጵያ በቅርቡ የጋዝ ምርትን ለገበያ እንደምታቀርብ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) አስታወቁ።
Next article“1 ነጥብ 5 ቢሊየን ኩንታል ምርት መሠብሠብ ተችሏል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)