ኢትዮጵያ በቅርቡ የጋዝ ምርትን ለገበያ እንደምታቀርብ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) አስታወቁ።

18

ባሕር ዳር: ሰኔ 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሠጡ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው ኢትዮጵያ የጋዝ ምርትን በቅርቡ ለገበያ እንደምታቀርብም ተናግረዋል። የጋዝ ፕሮጄክቱ የመጀመሪያው ምዕራፍ ሥራ መጠናቀቁንም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በቅርቡ የማዳበሪያ ፋብሪካ መሥራት እንደምትጀምርም ገልጸዋል። ከ40 ወራት በኋላ ጨርሳ ታስመርቃለች ነው ያሉት። በእነዚህ ሥራዎች የኢትዮጵያ ዕድገት ከታቀደው በላይ ሊኾን እንደሚችል አንስተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“8 ነጥብ 4 በመቶ አጠቃላይ እድገት ለማስመዝገብ እየተሠራ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next articleየሰላም ግንባታ ጥረቶችን እና የልማት እንቅስቃሴዎችን ለማጠናከር ያለመ ምክክር በወግዲ ወረዳ ተካሄደ።