የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጠየቁ።

13

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት፣ 42ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው። በጉባኤው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በማኅበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የተለያዩ አስተያየቶችን እና ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) አንስተዋል። ከተነሱ ጉዳዮች መካከል በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በትግራይ ክልሎች ያሉ ግጭቶችን ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት አድንቀዋል።

በሀገሪቱ እየተከናወነ የሚገኘው የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ማብራሪያ እንዲሰጥበትም ተጠይቋል። ሙስና የሀገሪቱ ማነቆ በመኾኑ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር እየተሠራ ያለውን ተጨባጭ ሥራም የምክር ቤት አባላቱ አንስተዋል።

በተለየዩ ከተሞች እየተሠራ ስላለው የኮሪደር ልማት በአፈፃጸሙ ዙሪያ የምክር ቤት አባላት ጥያቄ አንስተዋል። የኑሮ ውድነት በማኅበረሰቡ ላይ እያደረሰ ያለውን ጫና እንዴት ማቃለል እንደሚቻልም ተነስቷል። በመንገድ እና በጤና ተቋማት ግንባታ ዙሪያ ስለሚስተዋሉ ችግሮች መፍትሄ ይሰጥ ዘንድ፣ በተፎካካሪ ፓርቲዎች አባላት የሚደርሰው እንግልት እና ወከባ ሊቆም እንደሚገባም ተጠይቋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየጦርነት ጠማቂ ፖለቲከኞች መጋለጥ እንደሚገባቸው እና የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያወግዛቸው ማድረግ ይገባል።
Next articleከትምህርት ገበታ የራቁ ተማሪዎችን ለመመለስ ምን እየተሠራ ነው?