ምክትል ርእሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) በመካነ ሰላም ከተማ ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር እየተወያዩ ነው።

16

ደሴ: ሰኔ 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ርእሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) ከመካነ ሰላም ከተማ እና ቦረና ወረዳ ነዋሪዎች ጋር በወቅታዊ የሰላም እና የልማት ጉዳዮች ዙሪያ እየተወያዩ ነው።

“ሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ባለው ውይይት የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች እና ልዩ ልዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው።

በውይይቱ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴንን (ዶ.ር) ጨምሮ የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳዳሪ አሊ መኮንን፣ በብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ወሎ ዞን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋ ዳኛው እና ሌሎች የመንግሥት እና የፀጥታ ኀላፊዎች ጋር ተገኝተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሰበዓዊ ከኾነው አገልግሎት ዋነኛው እና ቀዳሚው ደም መለገስ ነው።
Next articleየኮምቦልቻ ከተማን ውበት የገለጠው የኮሪደር ልማት