ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) በመካነ ሰላም ከተማ የሚገነቡ የመሠረተ ልማት ሥራዎችን ጎበኙ።

16

ደሴ: ሰኔ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) በደቡብ ወሎ ዞን መካነ ሰላም ከተማ የሚገነቡ የመሠረተ ልማት ሥራዎችን ጎብኝቷል።

ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ በተለይም ለአሚኮ እንዳሉት በከተማዋ የሚሠሩ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ሕዝቡ እና መንግሥት ተናብበው እየሠሩ መኾናቸውን የሚያሳይ ነው። ልማት ሰላምን ይፈልጋል ያሉት ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ የአካባቢው ሕዝብ ሰላሙን ለማስጠበቅ በጋራ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

ሕዝቡ ሰላሙን ሲያስጠብቅ የክልሉ መንግሥት የአካባቢውን የመልማት ፍላጎት ደረጃ በደረጃ ይመልሳልም ነው ያሉት። ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩን ጨምሮ የክልል እና የዞን የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎቹ የሆስፒታል ማስፋፊያ ግንባታ፣ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ ሥራዎች እና ሌሎች የመሠረተ ልማት ሥራዎችን ነው የተመለከቱት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኦፓል ልማት ዘርፉ ከአመራረት እስከ ግብይት ሂደት ውስብስብ ችግሮች አሉበት።
Next articleበ25 ከተሞች አዲስ የባንክ አካውንት ለመክፈት የፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ አስገዳጅ ኾነ።