
ደሴ፡ ሰኔ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በደቡብ ወሎ ዞን ከገነቴ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ የደቡብ ወሎ ዞን አሥተዳዳሪ አሊ መኮነን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በዚህ ወቅት የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ጥያቄዎች ማንሳት ቅንጦት እንደኾነባቸው አንስተዋል ። ጽንፈኛ ኀይሉ እያደረሰ ካለው የምጣኔ ሀብት ችግር ባሻገር ልጆቻችን እንዳይማሩ እና እንዳንኖር እያደረገ ነው ብለዋል።
የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየፈጸመባቸው መኾኑንም ገልጸዋል። የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) ጽንፈኛ ቡድኑ ከአማራ ሕዝብ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር አቅዶ እየሠራ መኾኑን አስገንዝበዋል ። የጽንፈኛ ቡድኑን እኩይ ዓላማ ለማስቀረት እና የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ ሕዝቡ ከመንግሥት ጋር ተባብሮ መሥራት አለበት ብለዋል ።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን