የሰሜን ጎንደር ዞን በመኸር ዓመቱ ከ3 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሠብሠብ አቅዶ እየሠራ ነው።

15

ደባርቅ: ሰኔ 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የዞኑ ግብርና መምሪያ በምርት ዘመኑ ከ3 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሠብሠብ አቅዶ እየሠራ እንደሚገኝም ገልጿል።የሰሜን ጎንደር ግብርና መምሪያ ምክትል ኀላፊ ዮሐንስ ይግዛው ከ100 ሺህ ኩንታል በላይ አፈር ማዳበሪያ ለማሰራጨት መታቀዱን ገልጸዋል።እስካኹን ከ40 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ እና ከ7 ሺህ ኩንታል በላይ ምርጥ ዘር ማሰራጨት መቻሉን ገልጸዋል፡፡

ከሰው ሠራሽ የአፈር ማዳበሪያ በተጨማሪ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሜትሪክ ኩብ በላይ በበጋ የተዘጋጀ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ለአገልግሎት እንዲውል መደረጉን አብራርተዋል፡፡ እስካኹን በተሠሩ ሥራዎች ከ40 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በዘር መሸፈን ተችሏል ብለዋል፡፡ ግብዓት በማጓጓዝ ሂደት የነዳጅ እጥረት እና የጸጥታ ችግሮች ፈታኝ እንደነበሩ አስታውሰዋል፡፡

በዞኑ በሚገኙ ሁለት ወረዳዎች ዘር ከተዘራ በኋላ የዝናብ መቆራረጥ አጋጥሞ የነበረ ቢኾንም በአኹኑ ወቅት ጥሩ የሚባል የዝናብ መጠን መኖሩን አቶ ዮሐንስ ገልጸዋል፡፡ በቀጣይም አርሶ አደሮ ከባለሙያዎች የሚሰጡ የግብርና ምክር ሀሳቦችን በተግባር ላይ በማዋል ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን ቀድሞ መከላከል እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleሀገራዊ ቅርሶች በሕግ ዐይን።
Next articleበአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ከ5 መቶ ሺህ በላይ የማኅበረሰብ ክፍሎችን በበጎ ፈቃድ ሥራ ለማሳተፍ እየተሠራ ነው።