
ባሕር ዳር: ሰኔ 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በውጭ ሀገራት የሚሠሩ ኢትዮጵያውያንን መብት፣ ደኅንነት እና ዘላቂ ጥቅም ያስጠብቃል ያለውን የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ረቂቅ አዋጅ አዘጋጅቶ አቅርቧል፡፡
ረቂቅ አዋጁ ግንቦት 21/2017 ዓ.ም ለሚኒስትሮች ምርቤት ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ መወሰኑ ይታወቃል፡፡የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም ረቂቅ አዋጁን መርምሮ ሰኔ 5/2017 ዓ.ም ለሰው ኃይል ሥራ ሥምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቶታል፡፡ ረቂቅ አዋጁ ሲጸድቅ የዜጎችን መብት፣ ደኅንነት እና ዘላቂ ተጠቃሚነት ያረጋግጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ደረጃ ያለው የፍቃድ አሰጣጥ ሥርዓት፣ የተቀነሰ የገንዘብ ዋስትና፣ ጥብቅ የፋይናንስ ቁጥጥሮች፣ ግልጽ እና ከሰው ንክኪ ነፃ የኾነ የአሠራር ሥርዓት የረቂቅ አዋጁ ቁልፍ ማሻሻያዎች መኾናቸው ተጠቅሷል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን