በተቀናጀ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ሥራዎች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ይሠራል።

14

ባሕር ዳር: ሰኔ 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤቱ ኅላፊ መላክነሽ ኃይሉ የምግብ ዋስትና መርሐ ግብር በአረንጓዴ ልማት፣ በከተማ ጽዳት እና ውበት እንዲሁም በከተማ ግብርና ተወስኖ መቆየቱን ገልጸዋል።

በ2018 በጀት ዓመት በተቀናጀ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ሥራ እንሠራለን ብለዋል። በዚህም ከተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ባሻገር የሴፊቲኔት ተጠቃሚ ወገኖች በኢኮኖሚ እንዲደረጅ ያደርጋል። በተፋሰሱ አካባቢ ነዋሪዎችንም ሁለንተናዊ ተጠቃሚ ያደርጋል ነው ያሉት።

በተለይም የከተማ አሥተዳደሩን የገጠር ቀበሌዎች ልማት በማጎልበት የጎብኝዎች መዳረሻ ለማድረግ መታቀዱን ገልጸዋል። የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራው ሥነ ምህዳራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው ጉልህ መኾኑን ነው የገለጹት።ሥራው ስኬታማ ይኾን ዘንድ ከከተማ አሥተዳደሩ ግብርና መምሪያና መሰል ባለ ድርሻ አካላት ጋር መክረናል ያሉት ኅላፊዋ በተፋሰሱ አካባቢ የሚኖሩ ወገኖች የድርሻቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleበምዕራብ ጎንደር ዞን ከ890 ሺህ በላይ ችግኞች ለተከላ ዝግጁ ኾነዋል።
Next articleበባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር በከተማ ግብርና ሥራ የተሰማሩ ሴቶች ውጤታማ መኾናቸውን ተናገሩ፡፡